ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በ6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ በተለይ በመራጨች ምዝገባ ሂደት ማህበሩ ስልጠና ሰጥቶ በአዲስ አበባ በ120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ባሰማራቸዉ ታዛቢዎቹ ያገኛቸዉን ግኝቶች አስመልክቶች የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ) ስልጠና የወሰዱ አና ብቁ የሆኑ 18 ታዛቢዎችን በአዲስ አበባ በሚገኙ 120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች በማሰማራት ከሚያዚያ 20 እስከ ግንቦት 4 2013 ዓ.ም በመዲናዋ የተካሄደዉን የመራጮች ምዝገባ ሂደትን እንዲታዘቡ አድርጓል፡፡ ታዛቢዎቹ በነዚህ የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ያለዉን የመራጮች ምዝገባ ዝግጅት ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊነት ፣ በመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች በሚሰሩ ሰራተኞች መካከል ያለዉን የሥርዓተ-ፃታ ሚዛን ፣ ለመራጮች ትምህርት የመስጠት እንቅስቃሴዎችን እና በመራጮች ምዝገባ ሂደት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን አስመልክቶ ምልከታ አድርገዋል (ታዝበዋል)፡፡

ከተገኙ ምልከታዎች መካከል፡-

  • የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ) በአዲስ አበባ ምልከታ ያደረገባቸዉ ሁሉም የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች የሚገኙት ከተማ ዉስጥ ነበር፡፡ አብዛሃኞቹ የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች መደበኛ በሚባለዉ ስር የሚካተቱ ሲሆን አንድ ብቻ ወታደራዊ ካምፕ ዉስጥ የነበረ የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ በምልከታቸዉ ተካትቷል፡፡
  • የ ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች ከመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ ሃላፊዎች ባገኙት መረጃ መሰረት ሴቶች እና ወንዶች ተመጣጣኝ ወይም እኩል በሚባል ደረጃ የመራጭነት ምዝገባን ታዛቢዎቹ በነበራቸዉ የምልከታ ቀናት ዉስጥ አከናዉነዋል፡፡ በተመሳሳይ የምልከታ ቀናት ለመራጮች ትምህርት የሚሰጡ ቁሳቁሶችን ለሴቶች ተደራሽ በማድረግ ረገድ መመልከት ወይም መስማት የቻሉት ጥቂቶቹ (5) የ ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች ብቻ ናቸዉ፡፡
  • እንደ የ ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች ምልከታ ከ 120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች መካከል አብዝሃኛዎቹ ሴቶች በቀላሉ እና በጣም በቀላሉ ለማለት በሚያስችል መልኩ ተጉዘዉ/ሄደዉ ማግኘት የሚችሏቸዉ ነበሩ፡፡ 18 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ላይ ለመድረስ ግን አስቸጋሪ እና በጣም አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ በአጠቃላይ ታዛቢዎች ምልከታ ካደረጉባቸዉ ከ120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች መካከል የአካል ጉዳት ወይም እንደልብ እንቅስቃሴ ማድረግ ለማይችሉ ፣ ለአረጋዉያን እንዲሁም ሕፃናትን ይዘዉ ለሚሄዱ ሰዎች 94ቱ በቀላላ መድረስ ወይም መግባት የሚችሉባቸዉ ሆነዉ አግኝተዋቸዋል፡፡
  • መራጮችን በመመዝገብ የሰስራ ሂደት ዉስጥ ከተሰማሩ ሃላፊዎች መካከል የሴቶች ዉክልና ወይም ተሳትፎ ዝቅተኛ ነበር፡፡ ምልከታ ካደረግንባቸዉ ጣቢያዎች መካከል ሩብ ያክለሉ ላይ ወንዶች ብቻ በስራ ሂደቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ግማሽ ያክሉ የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ላይ ደግሞ አንድ (1) ብቻ ሴት ተሳታፊዎች በስራ ሂደቶች ተሳትፈዋል፡፡ በተጨማሪም በአጠቃላይ ምልከታ ካደረግንባቸዉ 120 ጣቢያዎች መካከል 28% ብቻ በሊቀመንበርነት ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
  • የ ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ ምልከታ ካደረገባቸዉ ጣቢያዎች መካከል ሁሉም በሚባል ደረጃ አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች የተሟሉላቸዉ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን አብዝሃኛዉ ብለን ከምንገልፀዉ በላይ የሆኑት ጣቢያዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚረዱ ቁሳቁሰች መካከል ቢያንስ አንዱ ይጎድለቸዉ ነበር፡፡

በ ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ ምልከታ ከተደረገባቸዉ ጣቢያዎች መካከል ከግማሽ በላይ በሚሆኑት ላይ የሚሰሩ አስፈፃሚዎች ወይም የመራጮች ምዝገባ ሰራተኞች ሁሉም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ያደረጉ ሲሆን አንድ ሦስተኛ በሚሆኑት ጣቢያዎች ደግሞ የተወሰኑት ሰራተኞች እና ሃላፊዎች ብቻ ጭምብል አድርገዋል፡፡ ነገር ግን የ ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ ምልከታ ካደረገባቸዉ አጠቃላይ ጣቢያዎች መካከል አምስቱ (5) ላይ አንዳቸዉም ሃላፊዎች ወይም ሰራተኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እናዳለደረጉ ምልከታ ተደርጓል፡፡

Text Widget

Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Donec sed odio dui. Etiam porta sem malesuada.

Tag Cloud

Related Posts

ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች በተካሄደዉ ምርጫ በኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች በተመዘገቡ ምልከታዎች ዙሪያ ያቀረበዉ ቀዳሚ ምለጫ

ኢትዮጵያ እንደሚታወቀዉ 6ኛዉን ሃገረራዊ እና ክልላወዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በስድስተት (6) ክልሎች እና ሁለት (2) ከተማ አስተዳደሮች...

ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የተፈፀሙ የሃይል እርምጃዎችን (ጥቃቶችን) በሚመለከት ባደረገዉ ምልከታ ያገኛቸዉን ግኝቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ያካተተ መግለጫ ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር የ2013 ዓ.ም 6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ አካታችነትንና በተለይም በሴቶች ሙሉ እና እኩል ተሳትፎ ዙሪያ አስተዋፅኦ ለማበርከት...

ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ

5ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበል የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በዛሬው እለት ባዘጋጀው የችግኝ መትከል መርሀ...

Leave a Reply