ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የተፈፀሙ የሃይል እርምጃዎችን (ጥቃቶችን) በሚመለከት ባደረገዉ ምልከታ ያገኛቸዉን ግኝቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ያካተተ መግለጫ ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር የ2013 ዓ.ም 6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ አካታችነትንና በተለይም በሴቶች ሙሉ እና እኩል ተሳትፎ ዙሪያ አስተዋፅኦ ለማበርከት በቅድመ-ምርጫ ወቅት እና በምርጫ ቀን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን በሚመለከት ምልከታ (የመታዘብ ስራ) አከናዉኗል፡፡ ምልከታዉ ሴት መራጮች ፣ ታዛቢዎች ፣ የምርጫ ጣቢያ ሰራተኞች ፣ እጩ ተመራጮች እና የምርጫ ጣቢያ ታዛቢዎች በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶች የተነሳ እንዴት ተፅዕኖ እንደደረሰባቸዉ ምልከታ አድርጓል፡፡ የምልከታ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች አላማ ባጠቃላይ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶች ዙሪያ በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ ግንዛቤ እንዲስፋፋ እና በባለድርሻ አካላት ዘንድ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ ሊፈፀሙ ስለሚችሉ ጥቃቶች ግንዛቤ በማስፋፋት ወደፊት በሚደረጉ ምርጫዎች ለሴቶች ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነዉ፡፡

ማህበሩ 150 የቅድመ-ምርጫ ሂደቶችን የሚታዘቡ የረዥም ጊዜ ታዛቢዎችን እና 130 የድምፅ መስጫ (የምርጫ)ቀንን የሚታዘቡ ታዛቢዎችን ቀጥሮ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የታዛቢዎች የረዠም ጊዜ ምልከታ ለመጀመር ግን ምርጫ ቦርድ ለታዛቢዎች የሚሰጠዉ የዕዉቅና ፈቃድ (ባጅ) በመዘግየቱ እና በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የነበረዉ የፀጥታ ሁኔታ ታዛቢዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱና የምልከታ ስራቸዉን በታቀደለት መሰረት እንዲጀምሩ የሚያስችል ባለመሆኑ የተነሳ የመታዘብ ስራችን ላይ ገደብ አሳድሯል፡፡ በብዙ ሃገራት ማህበረሰቦች ዘንድ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እየተለመዱ መጥተዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም ከምርጫ ጋር ተያይዘዉ የሚፈፀሙትን ጨምሮ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የሃይል እርምጃዎችን መመዝገብ እና ማመልከት ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ በታች የተቀመጡት የምልከታ ግኝቶች በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ በተካሄደዉ ሃገር ዓቀፍ ምርጫ ከተከሰቱ በሴቶች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች መካከል የኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ያሰማራቸዉ ታዛቢዎች በተገደበ የምልከታ ጊዜ ዉስጥ የተመለከቷቸዉ ወይም የሰሟዋቸዉ እና ወደ ማህበሩ ዋናዉ ቢሮ የመረጃ መሰብሰቢያ ቋት ማዕከል ልከዋቸዉ የመጣራት ሂደት የተደረገባቸዉ ናቸዉ፡፡

ቅድመ-ምርጫ ሂደቶች ላይ ምልከታ ያደረጉ የረዥም ጊዜ ታዛቢዎች 341 መጠይቆችን ሞልተዉ በማጠናቀቅ ያቀረቡ ሲሆን በሴቶች ሙሉ እና ዉጤታማ ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያስከትሉ የቻሉ ጥቃቶችን በተመለከቱበት እና በሰሙበት ወቅት ሞልተዉ ያጠናቀቋቸዉን 100 የወሳኝ ክስተቶችን ግኝቶች በወሳኝ ክስተቶች መሙያ መጠይቅ ላይ ሞልተዉ መላክ ችለዋል፡ ፡ ከነዚህ በኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች በቅድመ-ምርጫ ወቅት ከተመዘገቡት ክስተቶች መካከል በሴቶች ላይ የተፈፀመ ዛቻ እና ማስፈራራት በስፋት የታየ እና የተመዘገበ የጥቃት አይነት (4) ነበር ፡፡

በተጨማሪም የኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች 7 የወሲባዊ ትንኮሳ ድርጊቶችን ፤ 2 አካላዊ ጥቃቶችን እና 2 በፀጥታ አስከባሪ አካለት የተፈፀመ የሴት ዕጩ ተወዳደሪዎችን የምረጡኝ ዘመቻ ያስተጓጎሉ ድርጊቶችን መታዘብ ችለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሴት መራጮች በመራጮች ትምህርት ወይም በምርጫ ዘመቻዎች እንዳይሳተፉ እና ለመሳተፍ ተስፋ እንዲቆርጡ የተደረጉ (8) ድርጊቶች ተመዝግበዋል፡፡ እንዲሁም ሴተች በምረጡኝ ዘመቻዎች እንዳይካተቱ የሚያደርግ (8) ክስተቶች ተመዝግበዉ ነበር፡ ፡ የኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና የአካባቢ አስተዳደር ባለስልጣናት ሴቶችን በማባበል ድምፅ እንዲሰጧቸዉ የተሞከሩ 10 ክስተቶችን ሪፖርት አድርገዋል፡፡ የኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች በተጨማሪም የቅድመ-ምርጫ ሂደቶች አካታችነትንና የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎን ሁኔታ ገምግመዋል፡፡ ታዛቢዎቹ 39 አካል ጉዳተኞች ወደ ምርጫ ጣቢያ ለመግባት አስቸጋሪ የነበሩ እና በምርጫ አስፈፃሚዎች የተፈፀባቸዉን ያልተገባ አያያዝ ታዝበዋል ወይም አቤቱታዎችን ሰምተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በድምፅ መስጫ ቀን የድምፅ አሰጣጥ ሂደቶችን እና በምርጫዉ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመታዘብ 369 የምርጫ ጣቢያዎችን መጎብኘት የቻሉ 130 ታዛቢዎችን አሰማርቶ ነበር፡፡ ሁሉም የተሰማሩት ታዛቢዎች የምርጫ ቀን መጠይቆችን አጠናቀዉ የሞሉ ሲሆን 100 የወሳኝ ክስተቶች መሞያ መጠይቆችንም አጠናቀዉ በመሙላት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ምልከታ ከተደረገባቸዉ የምርጫ ጣቢያዎች 80% ሚሆኑት ላይ ሰልፎች የተስተዋሉ ሲሆን 58% በሚሆኑት ላይ ደግሞ ለወንዶች እና ሴቶች የተለዩ የሰልፍ መስመሮች ባለመኖራቸዉ በሴቶች ላይ ሊፈፀም የሚችል የፆታዊ ትንኮሳ ስጋትን ከፍ ሊያደርገዉ ችሏል፡፡

በኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች ምልከታ የተደረገባቸዉ አንዳንድ የምርጫ መታዘብ ግኝቶች የተመዘገቡት ተሰልፈዉ በነበሩ ሴት መራጮች ላይ የተፈፀሙትን ወሲባዊ ትንኮሳዎች ያክትታሉ፡፡ በኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች ምልከታ በተደረገባቸዉ ጣቢያዎችዉስጥ የሴቶች ዉክልና አናሳ የነበረ ሲሆን ከምርጫ ጣቢያዎቹ 83% ወንድ ሊቀመንበሮች የነበራቸዉ ሲሆን 18% ብቻ በሚሆኑት ሴት ሊቀመንበሮችን አስተዉለዋል፡፡

የማህበሩ ታዛቢዎች በምርጫዉ ቀን በሴቶች ላይ የተፈፀሙ 13 ጥቃቶችን የመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል አካላዊ ጥቃት (2) ፤ ወሲባዊ ትንኮሳ (11) እንዲሁም ስነ-ልቦናዊ ጥቃት (2) ተመዝግበዋል፡፡ የድምፅ መስጫ ካርዶች እጥረት ያጋጠማቸዉ ጣቢያዎችም በድምፅ መስጫ ቀኑ የኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች ከመዘገቧቸዉ (17ቱ) እጅግ በጣም አሳሳቢ ከሚባሉት ክስተቶች መካከል የሚመደቡ ነበሩ፡፡

ኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች በተጨማሪም እገዛ የሚያስፈልጋቸዉ የማይመስሉ ሴት መራጮች በምርጫ አስፈፃሚ አካላት እገዛ እንደተደረገላቸዉ ምልከታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም (3) ለመምረጥ መስፈርቱን ያላሟሉወንዶች እና (2) ለመምረጥ መስፈርቱን ያላሟሉ ሴቶች ድምፅ እንዲሰጡ እንደተፈቀደላቸዉ ታዝበዋል፡፡ በምርጫ ጣቢያዎች መገኘት ያልተፈቀደላቸዉ (5) ግለሰቦች በጣቢያዎች እንደተገኙ ፤ በ(3) የምርጫ ጣቢያዎች እንደተሰረዘ እና (4) ምርጫዉን የመታዘብ ስራን እንዳያከናዉን የታዛቢዎች መብት እንደተነፈገ ታዝበዋል፡፡ አንድ የኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢ ደግሞ ቆጠራ እስኪጠናቀቅ በሚል ያለፈቃዱ ያለምግብ እና ዉሃ ሌሊቱን እንዲያሳልፍ እና እስከሚቀጥለዉ ቀን ድረስ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የተፈፀሙ የሃይል እርምጃዎችን (ጥቃቶችን) በሚመለከት ባደረገዉ ምልከታ ያገኛቸዉን ግኝቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ያካተተ ሪፖርት የድህረ-ምርጫ ሂደቶችም በተጠናቀቁ ጊዜ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

Text Widget

Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Donec sed odio dui. Etiam porta sem malesuada.

Tag Cloud

Related Posts

ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች በተካሄደዉ ምርጫ በኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች በተመዘገቡ ምልከታዎች ዙሪያ ያቀረበዉ ቀዳሚ ምለጫ

ኢትዮጵያ እንደሚታወቀዉ 6ኛዉን ሃገረራዊ እና ክልላወዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በስድስተት (6) ክልሎች እና ሁለት (2) ከተማ አስተዳደሮች...

ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በ6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ በተለይ በመራጨች ምዝገባ ሂደት ማህበሩ ስልጠና ሰጥቶ በአዲስ አበባ በ120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ባሰማራቸዉ ታዛቢዎቹ ያገኛቸዉን ግኝቶች አስመልክቶች የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ) ስልጠና የወሰዱ አና ብቁ የሆኑ 18 ታዛቢዎችን በአዲስ አበባ በሚገኙ 120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች...

ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ

5ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበል የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በዛሬው እለት ባዘጋጀው የችግኝ መትከል መርሀ...

Leave a Reply