ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች በተካሄደዉ ምርጫ በኢ.ህ.ባ.ሴ.ማ ታዛቢዎች በተመዘገቡ ምልከታዎች ዙሪያ ያቀረበዉ ቀዳሚ ምለጫ

ኢትዮጵያ እንደሚታወቀዉ 6ኛዉን ሃገረራዊ እና ክልላወዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በስድስተት (6) ክልሎች እና ሁለት (2) ከተማ አስተዳደሮች አካሂዳለች፡፡ ነግር ግን በፀጥታ ችግሮች ፣ በምርጫ ሂደት አስተዳደር እና አሰራር ክፍተቶች ምክንያት በተወሰኑ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለይም በሶማሌና ሐረሪ ክልሎች ምርጫ ባለመካሄዱ የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም መደረጉ የታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጷጉሜ 1 2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተደረገባቸዉ አካባቢዎች ምርጫ እንደሚካሄድ ያሳወቀ ቢሆንም የድምፅ መስጫ ቀኑ ለሁለተኛ ጊዜ እንደተራዘመ በማሳወቅ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲራዘም የተደረገዉ ምርጫ እንደሚካሄድ እንዲሁም በተወሰኑ የደቡብ ብሔርበሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካባቢዎች ምርጫ አና የህዝብ ዉሳኔ አሰጣጥ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደዉ 6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ ታዛቢዎችን በመመልመልና በማሰልጠን ባሰማራቸዉ ታዛቢዎች አማካኝነት የምርጫ ሂደቱ አካታችነትንና በተለይም የሴቶችን ሙሉ እና እኩል ተሳትፎ መቃኘት የሚያስችል ምልከታ (የመታዘብ ስራ) አከናዉኗል፡፡ ማህበሩ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶችን በሚመለከት በሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደዉ ምርጫ ምልከታ የሚያደርጉ 23 ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎችን ከአካባቢዎቹ በመመልመል አሰልጥኖ አሰማርቷል፡፡ ታዛቢዎቹ በድምፅ መስጫዉ ቀን መራጮች ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ሲደርሱ ጀምሮ ፣ በድምፅ መስጠት ሂደቶች ፣ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን መዝጊያ ሂደት እና ወሳኝ ክስተቶችን በሚመለከት የሚኖራቸዉን ምልከታ መመዝገብ የሚያስችላቸዉ አራት ወጥ መጠይቆች ተዘጋጅተዋል፡፡ ይኽ የማህበሩ ቀዳሚ ሪፖርት የተዘጋጀዉ ታዛቢዎቹ በድምፅ መስጫዉ ቀን በምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋዉረዉ ምልከታ በማድረግ ሞልተዉ ባጠናቀቋቸዉ መጠይቆች መሰረት ነዉ፡፡ ታዛቢዎቹ በምርጫ ሂደት በሴቶች ላይ የሚፈፀምን ጥቃት አስመልክቶ በነበራቸዉ የመታዘብ ሂደት 22 መራጮች ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ሲደርሱ የተደረጉ ምልከታዎችን ፣ 59 በድምፅ መስጠት ሂደቶች ላይ የተደረጉ ምልከታዎችን እና 19 በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የመዝጊያ ሂደቶች የተደረጉ ምልከታዎችን በማድረግ መጠይቆችን ሞልተዉ ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ምልከታ ባደረጉባቸዉ የምርጫ ጣቢያዎች የተመለከቷቸዉን 4 (አራት)ወሳኝ ክስተቶች ሪፖርት አድርገዋል፡፡

Text Widget

Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Donec sed odio dui. Etiam porta sem malesuada.

Tag Cloud

Related Posts

ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የተፈፀሙ የሃይል እርምጃዎችን (ጥቃቶችን) በሚመለከት ባደረገዉ ምልከታ ያገኛቸዉን ግኝቶች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ያካተተ መግለጫ ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር የ2013 ዓ.ም 6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ አካታችነትንና በተለይም በሴቶች ሙሉ እና እኩል ተሳትፎ ዙሪያ አስተዋፅኦ ለማበርከት...

ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ በ6ኛዉ ሃገር-ዓቀፍ ምርጫ በተለይ በመራጨች ምዝገባ ሂደት ማህበሩ ስልጠና ሰጥቶ በአዲስ አበባ በ120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች ባሰማራቸዉ ታዛቢዎቹ ያገኛቸዉን ግኝቶች አስመልክቶች የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ) ስልጠና የወሰዱ አና ብቁ የሆኑ 18 ታዛቢዎችን በአዲስ አበባ በሚገኙ 120 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዎች...

ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ

5ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበል የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በዛሬው እለት ባዘጋጀው የችግኝ መትከል መርሀ...

Leave a Reply