5ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበል የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በዛሬው እለት ባዘጋጀው የችግኝ መትከል መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ተሳትፎ አድርጓል፡፡
በመርሀ ግብሩ መሰረትም ማህበሩ ሰራተኞቹን እና በጎፈቃደኛ አባላቶቹን በማስተባበር በዛሬው እለት ከጠዋቱ 1፡00ሰአት ጀምሮ በአዲስ አበባ እንጦጦ ፓርክ በመገኘት 100 ችግኞችን ገዝቶ በማስረከብ አረንጋዴ አሻራውን አኑሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል ድጋፍ እንዲደረግ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል ማህበሩ ከሰራተኞቹ ደሞዝ ላይ የተሰበሰበ የ50ሺብር ድጋፍ ለሀገር አቀፉ የኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከል ግብረሀይል ገቢ አድርጓል፡፡ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በመንግስት እየተደረገ ያለውን ከፍተኛ ርብርብ ማህበሩ እንደሚያደንቅ እየገለጸ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ማህበሩ በአረንጋዴ አሻራ እና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከል ስራ ላይ ተሳትፎ በማድረጉም የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ እየገለጸ ወደፊትም በሚደረጉ ሀገር አቀፍ ጥሪዎች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

