ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ

5ቢሊዮን ችግኝ በመትከል አረንጋዴ አሻራን የማሳረፍ ሀገራዊውን ጥሪን በመቀበል የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በዛሬው እለት ባዘጋጀው የችግኝ መትከል መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ተሳትፎ አድርጓል፡፡

በመርሀ ግብሩ መሰረትም ማህበሩ ሰራተኞቹን እና በጎፈቃደኛ አባላቶቹን በማስተባበር በዛሬው እለት ከጠዋቱ 1፡00ሰአት ጀምሮ በአዲስ አበባ እንጦጦ ፓርክ በመገኘት 100 ችግኞችን ገዝቶ በማስረከብ አረንጋዴ አሻራውን አኑሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል ድጋፍ እንዲደረግ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል ማህበሩ ከሰራተኞቹ ደሞዝ ላይ የተሰበሰበ የ50ሺብር ድጋፍ ለሀገር አቀፉ የኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከል ግብረሀይል ገቢ አድርጓል፡፡ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በመንግስት እየተደረገ ያለውን ከፍተኛ ርብርብ ማህበሩ እንደሚያደንቅ እየገለጸ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ማህበሩ በአረንጋዴ አሻራ እና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከል ስራ ላይ ተሳትፎ በማድረጉም የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ እየገለጸ ወደፊትም በሚደረጉ ሀገር አቀፍ ጥሪዎች ላይ ተሳትፎ ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

Text Widget

Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Nulla vitae elit libero, a pharetra augue. Donec sed odio dui. Etiam porta sem malesuada.

Tag Cloud

Related Posts

ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ያስተላለፉት መልዕክት ባለፈው እሁድ ጠዋት በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጊዜያዊ የሴቶች ማረፊያ ማዕከልን የመጎብኘት...

“Berchi” radio program is back

በርቺ!! Dear members, partners and our followers, “Berchi” radio program is back on air already and started to broadcast on...

በሴቶች ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጥቃት በሞራልም ሆነ በህግ አግባብ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ ተግባር ነው!!

በሴቶች ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጥቃት በሞራልም ሆነ በህግ አግባብ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ ተግባር ነው!! አለማችን ላይ እጅጉን ፈታኝ እየሆነ የመጣውንና በአገራችንም...

Leave a Reply